am_tn/ezr/07/21.md

2.8 KiB
Raw Permalink Blame History

አገናኝ መግለጫ

ይህ ንጉሥ አርጤክስስ ለዕዝራ የሰጠው ድንጋጌ ቀጣይ ክፍል ነው፡፡

ከወንዙ ማዶ ያለው ክፍለ ሐገር

ይህ ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተምዕራብ የሚገኘው ክፍለ ሀገር መጠሪያ ነው፡፡ ከሱሳ ከተማ አንፃር ከወንዙ ማዶ የሚገኝ ነው፡፡ ይህንን በዕዝራ 4፡10 እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡

ካህኑ ዕዝራ ከእናንተ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ በሙሉ ስጡት

ይህ በተግባራዊ ቅርጹ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ‹‹ካህኑ ዕዝራ ከእናንተ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ በሙሉ ስጡት››

በሙሉ ሊሰጠው ይገባል

‹‹በሙሉ›› የሚለው ሐረግ የሚወክለው ሥራውን ለመሥራት የሚያስፈልገውን መጠን ያህል የሚለውን ነው ‹‹የሚያስፈልገውን ያህል ሊሰጠው ይገባል፡፡››

አንድ መቶ መክሊት ብር

100 መክሊት ብር›› ይህንን ወደ ዘመናዊ መለኪያ መለወጥ ትችላለህ፡፡ 3,300 ኪሎ ግራም ሲልቨር

መቶ የቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ

ይህንን ወደ ዘመናዊ መለኪያ መለወጥ ትችላለህ፡፡ 22,000 ሊትር ስንዴ›› ወይም ‹‹ሃያ ሁለት ሊትር ስንዴ››

አንድ መቶ የባዶስ መስፈሪያ ዘይት

ይህንን ወደ ዘመናዊ መለኪያ መለወጥ ትችላለህ፡፡ 2,200 ሊትር ዘይት›› ወይም ሁለይ ሺህ ሊትር ዘይት››

የእርሱ ቤት

ይህ የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ነው፡፡

የእርሱ ቁጣ በመንግሥቴና በልጆቼ ላይ ስለምን ይመጣል?

ንጉሡ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው የእግዚአብሔር ቁጣ በእነርሱ ላይ እንዲመጣ ስለማይፈልግ ነው፡፡ ይሽም የሚያመለክተው ለዕዝራ የሚያስፈልገውን ካልሰጡ እግዚአብሔር መንግሥቱን እንደሚቀጣ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣ በመንግሥቴ እና በልጆቼ ላይ እንዲመጣ አንፈልግም

የእርሱ ቁጣ በመንግሥቴና በልጆቼ ላይ ስለምን ይመጣል?

የእግዚአብሔር ቁጣ የሚያመለክተው እግዚአብሔር እንደሚቀጣቸው ነው፡፡ ‹‹የእግዚአብሔር ቁጣ በመንግሥቴና በልጆቼ ላይ ስለምን ይመጣል? ወይም እነዚህን ነገሮች የማታደርጉ ከሆነ እግዚአብሔር መንግሥቴንና ልጆቼን ይቀጣ፡፡››