am_tn/ezr/06/21.md

2.0 KiB
Raw Permalink Blame History

በምድሩ ላይ ከሚኖሩ ካልነጹ ሰዎች ራሳቸውን ለዩ

ራስን ከርኩሰት መለየት የሚያሳየው የሚያረክሱ ነገሮችን አለማድረግን ነው፡፡ ‹‹እነርሱ በምድሩ ላይ የሚኖሩት ሰዎች የሚያደርጉትን ነገር ግን የሚያረክሳቸውን ነገር ማድረግ እምቢ አሉ››

የምድሩ ሰዎች ርኩሰት

እዚህ ላይ ‹‹ርኩሰት›› የሚያመለክተው በአግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን አለማግኘትን ነው፡፡ በምድሩ ላይ የሚኖሩት ሰዎች በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዳያገኙ ያደረጋቸው የሚያደርጉት ርኩሰት የሞላበት ሥራ ነው

እግዚአብሔርን መፈለግ

እግዚአብሔርን መፈለግ የሚያመለክተው እርሱን ለማወቅ፣ ለማምለክ፣ እና ለመታዘዝ መምረጥ ነው፡፡ እግዚአብሔርን መታዘዝ መምረጥ››

የአሦርን ንጉሥ ልብ መመለስ

የንጉሡን ልብ መመለስማለት ስለ ቤተ መቅደሱ ሥራ ሲያስብ ከነበረው የተለየ እንዲያስብ ማድረግ ነው፡፡ ‹‹የአሦር ንጉስ የነበረውን ዝንባሌ መለወጥ›› ወይም ‹‹የአሦርን ንጉሥ ፈቃደኛ ማድረግ››

ለቤቱ ሥራ እጃቸውን ያበረታ ዘንድ

ለሥራው እጃቸውን ያበረታ ዘንድ የሚለው የሚያመለክተው እንዲሠሩ መርዳትን ነው፡፡ የአሦር ንጉሥ ይህን ያደረገው እንዲሠሩ በመናገር እና ለሥራውም የሚያስፈልገውን ገንዘብ በመድጠት ነው፡፡ ቤቱን እንዲሠሩ ለመርዳት›› ወይም ቤቱን እንዲሠሩ ለማስቻል››

የቤቱ ሥራ

ይህ የሚያመለክተው የቤተ መቅደሱን ሥራ ነው፡፡