am_tn/ezr/06/08.md

1.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ

ይህ ንጉሥ ቂሮስ አይሁድ በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ እንዲገነቡ ያዘዘበት በዕዝራ 6፡3 ላይ የተገለጸው ዘገባ ቀጣይ ክፍል ነው፡፡

አስፈላጊው ገንዘብ በወንዙ ማዶ ከሚገኘው አገር ከንጉሡ የግብር ገቢ ለእነዚህ ሰዎች እንዲከፈል

ይህ እንደ አድራጊ ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ‹‹በወንዝ ማዶ ካለው አገር ከሚመጣው ግብር ከንጉሡ ገንዘብ ለእነዚህ ሰዎች ወጪውን በትጋት እንድትሰጡአቸው››

በወንዙ ማዶ ከሚገኘው አገር ከንጉሡ የግብር ገቢ

‹‹የንጉሡ የግብር ገቢ›› የሚያመለክተው ሰዎች ለንጉሡ የሚከፍሉትን ቀረጥ ነው፡፡ ‹‹ከወንዙ ማዶ ከለው አገር ከሚኖሩ ሰዎች ለንጉሡ በቀረጥ ከምትሰበስቡት ገንዘብ››

የሚያስፈልገውን

ይህ እንደ አድረጊ ቅርጽ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ‹‹የሚያስፈልጋቸውን››