am_tn/ezr/05/06.md

577 B

ይህ የደብዳቤው ግልባጥ ነው

ዕዝራ በቤተ መቅደሱ ስላለው የእነርሱ ሥራ ለንጉሡ ለዳርዮስ በተጻፈው ደብዳቤ ውስጥ ያለውን ይዘት ጠቅሶአል፡፡

ከወንዙ ማዶ ያለ ክፍለ ሐገር

ይህ ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተምዕራብ የሚገኘው ክፍለ ሀገር መጠሪያ ነው፡፡ ከሱሳ ከተማ አንፃር ከወንዙ ማዶ የሚገኝ ነው፡፡ ይህንን በዕዝራ 4፡10 እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡