am_tn/ezr/04/14.md

1.9 KiB
Raw Permalink Blame History

የቤተ መንግሥቱን ጨው እንበላለንና

ተቀባይነት ያላቸው ትርጉሞች፡- 1. ጸሐፊዎቹ ለንጉሡ ታማኞች ናቸው ወይም 2. ንጉሡ ለጸሐፊዎቹ የተለየ ክብር ሰጥቶአቸዋል፡፡ ‹‹እኛ ለአንተ ታማኞች ነን ወይም እኛን የአንተ ባለሟሎች በማድረግህ አክብረኸናል››

አመጸኛ ከተማ

ከተማዋ በውስጧ የሚኖሩትን ሰዎች ማንነት ትወክላለች፡- በዚህች ከተማ የሚኖሩ ሰዎች በአባትህም ላይ ያመጹ ነበሩ››

ከተማዋ ጠፍታ ነበር

ይህ በተግባራዊ ቅርጽ ሊተረጎም ይችላል፣ ከተማዋን ምን እንዳጠፋት ግልጽ ማድረግ ያስፈልግሃል፡፡ ‹‹ከተማዋ›› በውስጧ የሚኖሩትን ሰዎች ትወክላለች፡፡ ባቢሎናውያን ከተማዋን አጥፍተዋታል››

ይህች ከተማ ቅጥሮቿም ከተሠሩ

ይህ በተግባራዊ ቅርጽ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ይህን በዕዝራ 4፡13 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡ ‹‹ከተማዋንና ቅጥሮቿን ከገነቡ››

ለአንተ ምንም አይቀርልህም

እዚህ ላይ ‹‹ምንም›› የሚለው ቃል አይሁድ በንጉሡ ላይ ካመጹ ንጉሡ ብዙ የታክስ ገንዘብ እንደሚቀርበት የሚያሳይ የሚያጋንን ቃል ነው፡፡

ከወንዙ ማዶ ላለው ክፍለ ሐገር

ይህ ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተምዕራብ የሚገኘው ከተማ መጠሪያ ነው፡፡ ከሱሳ ከተማ አንፃር ከወንዙ ማዶ የሚገኝ ነው፡፡ ይህንንበዕዝራ 4፡10 እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት፡፡