am_tn/ezr/01/01.md

2.5 KiB
Raw Permalink Blame History

የመጀመሪያ ዓመት

ይህ የሚያሳየው የቂሮስን የመጀመሪያ የንግሥ ዓመት ነው፡፡

በኤርምያስ አፍ የተነገረውን ቃሉን እግዚአብሔር ፈጸመው

እዚህ ላይ ‹‹አፍ›› የሚለው የተነገረውን ለማለት ነው፡፡ ኤርምያስ እግዚአብሔር ያደርገዋል ብሎ የተነበየውን እግዚአብሔር አደረገው፡፡››

ያሕዌ

ይህ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ለሕዝቡ ራሱን የገለጠበት የእግዚአብሔር ስም ነው፡፡ ይህንን ስለመተርጎም በትራንስሌሽን ወርድ ፔጅ ላይ የተጻፈውን ተመልከት፡፡

እግዚአብሔር---የቂሮስን መንፈስ አስነሣ

እዚህ ላይ ቂሮስ የተገለጸው በመንፈሱ ነው፡፡ ይህም የሚናገረው እግዚአብሔር ቂሮስን መንፈሱን ‹‹በማስነሣት›› ፈቃዱን እንዲያደርግ መፈለጉን ነው፡፡ ‹‹እግዚአብሔር --- ቂሮስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ እንዲወድ አደረገው››

የቂሮስ አዋጅ በግዛቱ ሁሉ ላይ ተነገረ

አዋጁ የሚነገረውን መልእክት ምንነት የሚወክል ሲሆን ፣ በግዛቱ ሁሉ ላይ የሚለው ደግሞ በሚገዛው ምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ ይወክላል፡፡ ቂሮስ በመንግሥቱ ሁሉ ላይ አዋጅ አስነገረ፡፡››

የተጻፈውና የተነገረው ምንድን ነው

ይህ በአድራጊ ግስነት ሊተረጎም ይችላል፡፡ ቂሮስ ያወጀውን አዋጅ በሚገዛው ግዛት ሁሉ ላ ሰዎች እንዲደርስ ሌሎች ሰዎች እንደረዱት ተደርጎ ቢተረጎም የተሻለ ነው፡፡ ‹‹ቂሮስ የጻፈውን መልእክተኞቹ ሲያነቡ ሕዝቡ ሰሙአቸው››

የምድርን መንግሥታት ሁሉ

እዚህ ላይ ‹‹ሁሉ›› የሚለው ቃል የተጋነነ ነው፤ ቂሮስ የማይገዛቸውን ግዛቶች ሁሉ ያጠቃለለ ይመስላል፡፡

በይሁዳ --- ቤት ለእርሱ

ይህ ቤት ሕዝቡ እግዚአብሔርን የሚያመልኩበት ቤት እንደሆነ ግልፅ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በይሁዳ --- ሕዝቡ እግዚአብሔርን የሚያመልኩበት ቤት