am_tn/ezk/44/10.md

3.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለእስራኤል ቤት ያለውን መልዕክት ለሕዝቅኤል መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

ከእኔ ርቀው ሄደዋል…ከእኔ ኮብልለው ወደ ጣኦቶቻቸው ሄደዋል

"አንድ ሰው የሚኖርበት መንገድ የተገለጸው በመንገድ ላይ እንደመራመድ ተደርጎ ነው፡፡ "እኔን ማምለክ አቁመዋል… እኔ እንዲያደርጉ የምፈልገውን ማድረግ አቁመዋል፡፡ ይልቁንም፣ ጣኦቶቻቸውን ያመልካሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አገልጋዮች በተቀደሰው ስፍራዬ ናቸው

"አገልጋዮች በቤተ መቅደሴ ይሆንሉ"

የቤቱን በሮች መጠበቅ

"በቤቱ በር የጥበቃ ግዴታ ማከናወን"

በህዝቡ ፊት ቆመው ያገለግላሉ

"እነዚህ ሌዋውያን ህዝቡን ያገለግሉ ዘንድ በህዝቡ ፊት ይቆማሉ"

ለእስራኤል ቤት ኃጢአት የማሰናከያ ድንጋይ ይሆናሉ

በዚህ ሁኔታ ለዘመናት የያቆብ ትውልድ ለሆኑት እስራኤላውያን፣"ቤት" የሚለው ቃል፣ በቤቱ ለሚኖሩ ቤተሰቦች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ / ነው፡፡ይህ በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "እስራኤላውያኑ" ወይም "የእስራኤል ወገን ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የእስራኤል ቤት

"ቤት" የሚለው በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች በዚህ ሁኔታ ለብዙ ዘመናት የያዕቆብ ትውልድ ለሆኑ እስራኤላውያን ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "እስራኤላውያን" ወይም "የእስራኤል ወገን ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

መሃላ ለመማል እጄን አነሳለሁ

በእነዚያ ዘመናት አንድ ሰው ለማድረግ የማለውን ባይፈጽም እግዚአብሔር እንደሚቀጣው የተረዳ መሆኑን ለማሳየት ቀኝ እጁን ወደላይ ያነሳል፡፡ይህ በሕዝቅኤል 20፡6 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "እጄን አንስቼ እምላለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

በእነርሱ ላይ

"እኔ እቀጣቸዋለሁ"

ይህ የጌታ የያህዌ ትዕዛዝ ነው

ያህዌ ራሱን በስሙ የሚገልጸው/የሚምለው፤ የተናገረው እርግጠኛ መሆኑን ለማሳወቅ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ጌታ ያህዌ የተናገረው ይህንን ነው" ወይም "እኔ ጌታ ያህዌ የተናገርኩት ይህ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ቅጣታቸውን ይቀበላሉ

"ቅጣት" የሚለው ረቂቅ ስም በግስ መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እኔ በእርግጥ እቀጣቸዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)