am_tn/ezk/40/42.md

2.2 KiB

አራት ከተጠረበ ድንጋይ የተሰሩ ጠረጴዛዎች ነበሩ

እነዚህ መስዋዕቹ ከሚታረዱባቸው ስምንት ጠረጴዛዎች በግልጽ የተለዩ ነበሩ፡፡ ይህ ይበልጥ ግልጽ ተደርጎ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እንደዚሁም ደግሞ ከተጠረበ ድንጋይ የተሰሩ አራት ጠረጴዛዎች ነበሩ" ወይም "ከተጠረበ ድንጋይ የተሰሩ ሌሎች አራት ጠረጴዛዎች ነበሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ከተጠረበ ድንጋይ

"ከተጠረበ ድንጋይ የተሰሩ"

ክንዶች

በሕዝቅኤል 40፡5 ላይ እነዚህ "ረጅም" ክንዶች የሚለው እንዴት እንደ ተተረጎሙ ይመልከቱ፡፡

አንድ ክንድ ተኩል

ወደ 0.8 ሜትር (መጽሐፍ ቅዱስ ሲጻፍ የርቀት መለኪያ የነበሩ የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ከንድ

ወደ ግማሽ ሜትር ያህል

በመተላለፊያው ዙሪያ ቁመታቸው የእጅ መዳፍ የሚያሀል ሁለት ጣት ያላው ሜንጦዎች ተሰቅለዋል

"በመተላለፊያው ሁሉ ዙሪያ፣ ሰዎች የእጅ መዳፍ ርዝማኔ ያላቸው፣ እያንዳንዳቸው ባለ ሁለት ጣት የሆኑ ሜንጦዎችን አንጠልጥለዋል"

ሁለት ጣት ያላቸው ሜንጦዎች

ሁለት ረጃጅም የታጠፈ ጫፍ ያላቸው ሰዎች የተለያዩ ነገሮችን የሚሰቅሉባቸው እቃዎች

ቁመቱ የእጅ መዳፍ የሚያክል

ወደ 8 ሳንቲ ሜትር የሚሆን (መጽሐፍ ቅዱስ ሲጻፍ የርቀት መለኪያ የነበሩ የሚለውን ይመልከቱ)

የመስዋዕቶቹ ስጋ በጠጴዛዎች ላይ ይቀመጣል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ለመስዋዕት የሚቀርበውን ስጋ በጠረጴዛዎች ላይ ያስቀምጣሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)