am_tn/ezk/40/17.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ቤተ መቅደሱን የከበቡ ሁለት ግድግዳዎች ነበሩ፡፡ ውጫዊው ግድግዳ ውጫዊውን አደባባይ ይከባል፣ በዚያ ውስጥ ደግሞ ውስጣዊው ግድግዳ ውስጣዊውን አደባባይ ይከባል፡፡ ውስጣዊው አደባባይ ከውስጣዊው ቅጥር ግቢ ከፍ ያለ ነበር፡፡ እያንዳንዱ ግድግዳ በስተ ምስራቅ፣ ሰሜን እና ደቡብ አቅጣጫዎች በሮች አሉት፡፡

ሰውየው ወደ ቤተ መቅደሱ ውጫዊ አደባባይ አመጣኝ

"ሰውየው ከቤተ መቅደሱ ውጫዊ ስፍራ ወደ ቤተ መቅደሱ ውጫዊ አደባባይ አመጣኝ"

ውጫዊ አደባባይ

ይህ በሕዝቅኤል 10፡5 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

እነሆ

እዚህ ስፍራ "እነሆ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሕዝቅኤል አስደሳች ነገር ማየቱን ነው፡፡

የእግረኛ መንገድ

ከአለት/ድንጋይ የተሰራ ጠፍጣፋ ወለል

ከእግረኛው መንገድ አጠገብ ሰላሳ ክፍሎች

"እናም በእረኛ መንገዱ ዙሪያ 30 ክፍሎች ነበሩ" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

እስከ… ድረስ ሄደ

"እስከ… ድረስ ሁሉ ሄደ"

የታችኛው መግቢያ ፊት እስከ ውስጣዊ በር ፊት ለፊት ድረስ

የታችኛው በር በውጫዊ አደባባይ ግድግዳ ላይ ሲሆን፣ ውስጣዊው በር በስስጣዊው አደባባይ ግድግዳ ላይ ነበር፡፡ "ውጫዊው በር ፊቱ እስከ ውስጣዊ በር ፊት"

አንድ መቶ ከንድ

ወደ 54 ሜትር የሚጠጋ (መጽሐፍ ቅዱስ ሲጻፍ የርቀት መለኪያ የነበሩ የሚለውን ይመልከቱ)

ክንዶች

በሕዝቅኤል 40፡5 ላይ እነዚህ "ረጅም" ክንዶች የሚለው እንዴት እንደ ተተረጎሙ ይመልከቱ፡፡