am_tn/ezk/40/03.md

2.4 KiB

እሱ ወደዚያ አመጣኝ

"ያህዌ ቤቶቹ/ህንጻዎቹ ወዳሉበት ስፍራ አመጣኝ"

እነሆ

ሕዝቅኤል በተመለከተው ተደንቆ ነበር

የእርሱ መልክ እንደ ነሐስ መልክ ነበር

"መልክ" የሚለው ረቂቅ ስም በግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "የሚገለጽበት መንገድ ነሐስ በሚገለጽበት መንገድ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

የላይነን/ሊኖ ገመድ

"ከላይነን/ሊኖ የተሰራ ገመድ፡፡" ይህ በጣም ረጅም ርቀትን ለመለካት የሚያገለግል መሳሪያ ነው

ላይነን/ሊኖ

ይህ የክር አይነት ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 9፡2 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ

መለኪያ ዘንግ

ይህ አጭር ርቀትን መለኪያ መሳሪያ ነው

የሰው ልጅ

"የሰብአዊ ፍጡር ልጅ" ወይም "የፍጥረታዊ ሰው ልጅ፡፡" እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ ብሎ የሚጠራው ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ እና ሀያል ነው፣ ሰዎች ግን እንዲህ አይደሉም፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ሟች የሆነ ሰው" ወይም "ሰብአዊ ፍጡር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

አይምሮህን ትኩረት ስጠው

የዚህ ፈሊጥ ትርጉም "ትኩረት አድርግ" ወይም "አስብ" ማለት ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእስራኤል ቤት

"ቤት" የሚለው በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች በዚህ ሁኔታ ለብዙ ዘመናት የያዕቆብ ትውልድ ለሆኑ እስራኤላውያን ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ይህ በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡ "እስራኤላውያን" ወይም "የእስራኤል ወገን ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)