am_tn/ezk/40/01.md

1.9 KiB

ሃያ አምስተኛ…አስረኛ…አስራ አራተኛ

እነዚህ ቃላት የ25፣ 10 እና 14 ተከታታይ ቁጥሮች ናቸው፡፡ (ተከታታይ ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

የእኛ ምርኮኞች

እዚህ ስፍራ "የእኛ" የሚለው የሚያመለክተው ባቢሎናውያን ንጉሥ ዮአኪንን አስገድደው ከኢየሩሳሌም ካስወጡበት ጊዜ አንስቶ በባቢሎን የነበሩትን ሕዝቅኤልን እና አስራኤላውያንን እንጂ አንባቢውን አይደለም፡፡ "እኛ ምርኮኛ ከሆንን በኋላ" ወይም "ባቢሎናውያን ወደ ባቢሎን ምርኮኛ አድርገው ከወሰዱን በኋላ" (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የአመቱ መጀመሪያ የወሩ አስረኛ ቀን

ይህ በዕብራውያን የወር አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር ነው፡፡ አስረኛው ቀን በአውሮፓውያን አቆጣጠር በሚያዚያ ነው፡፡ (የዕብራውያን ወሮች እና ተከታታይ ቁጥሮች የሚሉትን ይመልከቱ)

ከተማይቱ ተይዛ ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ባቢሎናውያን የኢየሩሳሌምን ከተማ ያዙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የያህዌ እጅ

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው የሚያመለክተው ያህዌ ለሕዝቅኤል ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ራዕይ ለማሳየት ያለውን ሀይል ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 1፡3 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

እሱ ወደ እረፍት አመጣኝ

"እሱ እኔን አስቀመጠኝ"