am_tn/ezk/39/28.md

2.4 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ለእስራኤል ስለሚሆነው ለሕዝቅኤል መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

ወደ ምርኮ እልካቸዋለሁ… ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ

ሕዝቅኤል በሚጽፍበት ጊዜ፣ እስራኤል ገና በባቢሎን ነበሩ

ከዚህ በኋላ ፊቴን ከእነርሱ አልመልስም

እዚህ ስፍራ "ፊቴን ከእንግዲህ አልሰውርም" የሚለው ፈሊጥ ሲሆን ትርጉሙ ያህዌ እስራኤልን ከእንግዲህ በባቢሎን በስደት አይተውም ማለት ነው፡፡ "ከዚህ በኋላ አልተዋቸውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእስራኤል ቤት ላይ መንፈሴን ሳፈስ

እዚህ ስፍራ መንፈሱን አብዝቶ መስጠት የተገለጸው መንፈስን እንደ "ማፍሰስ" ተደርጎ ነው፡፡ "መንፈሴን በልግስና ለእስራኤል ቤት ስሰጥ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእስራኤል ቤት

"ቤት" የሚለው በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች፣ በዚህ ሁኔታ ለብዙ ዘመናት የያዕቆብ ትውልድ ለሆኑ እስራኤላውያን ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ይህ በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡ "እስራኤላውያን" ወይም "የእስራኤል ወገን ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የጌታ የያህዌ ትዕዛዝ ነው

ያህዌ ራሱን በስሙ የሚገልጸው/የሚምለው፤ የተናገረው እርግጠኛ መሆኑን ለማሳወቅ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ጌታ ያህዌ የተናገረው ይህንን ነው" ወይም "እኔ ጌታ ያህዌ የተናገርኩት ይህ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)