am_tn/ezk/39/23.md

3.2 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ለእስራኤል ስለሚሆነው ለሕዝቅኤል መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

የእስራኤል ቤት

"ቤት" የሚለው በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች፣ በዚህ ሁኔታ ለብዙ ዘመናት የያዕቆብ ትውልድ ለሆኑ እስራኤላውያን ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ይህ በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡ "እስራኤላውያን" ወይም "የእስራኤል ወገን ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እኔን በመክዳት በፈጸሙት በደላቸው/ኃጢአት ምከንያት

"በደል/ኃጢአት" የሚለው ረቂቅ ስም በግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ኃጢአት ስለ ሰሩ እና ስለካዱኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ

እዚህ ስፍራ "ፊት" የሚያመለክተው የያህዌን እርዳታ እና ድጋፍ ነው፡፡ "እኔ እነርሱን መጠበቄን እና መንከባከቤን አቆማለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ለተቃማሚዎቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ሀይልን ያመለክታል፡፡ "በእነርሱ ጠላቶቻቸው ላይ ሀይል እሰጣለሁ/ ጠላቶቻቸው በእነርሱ ላይ ሀይል እንዲያገኙ አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሉም በሰይፍ ይወድቃሉ

እዚህ ስፍራ መውደቅ የሚወክለው መገደልን ሲሆን፣ ሰይፍ ደግሞ ጦርነትን ይወክላል፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 32፡23 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ጠላቶቻቸው ሁሉንም በጦርነት ገደሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ንጹህ አለመሆናቸው እና ኃጢአቶቻቸው

ይህ የሚገልጸው የሰዎቹን አስጸያፊ ባህሪይ ሲሆን ይህም የተገለጸው ልክ በአካል ንጹህ እንዳልሆኑ ተደርጎ ነው፡፡ እዚህ ስፍራ "ንጹህ አለመሆን" ማለት በመሰረቱ "ኃጢአት" እንደ ማለት ነው፡፡ "አስጸያፊ ባህሪያቸው እና ኃጢአታቸው" ወይም "ኃጢአቶቻቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ጥንድ ትርጉም የሚሉትን ይመልከቱ)