am_tn/ezk/39/21.md

2.1 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል ለእስራኤል ስለሚሆነው መልዕክት ይነግረዋል

በአገራት መሃል ክብሬን አደርጋለሁ

ያህዌ ስለ ክብሩ የሚናገረው በአገራት መሃል ሊመለከቱት በሚችሉት ስፍራ እንደሚያስቀምጠው አድርጎ ነው፡፡ "አገራት ክብሬን እንዲመለከቱ አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የምፈጽመው ፍርድ እና በላያቸው የማሳርፈው እጄ

እነዚህ ሁለቱም ሀረጎች ያህዌ በእስራኤል ላይ የሚያደርገውን ፍርድ ያመለክታሉ፤ ገለጻው የተደጋገመው ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ በአንድ ሀረግ ሊጠቃለል ይችላል፡፡ "በእነርሱ ላይ የምፈርድበት መንገድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

እጄ

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ የሚያመለክተው ለቅጣት ያህዌ የሚጠቀምበትን ሀይል ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በእነርሱ ላይ

"በጎግ እና በሰራዊቱ ላይ"

የእስራኤል ቤት

"ቤት" የሚለው በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች በዚህ ሁኔታ ለብዙ ዘመናት የያዕቆብ ትውልድ ለሆኑ እስራኤላውያን ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ይህ በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡ "እስራኤላውያን" ወይም "የእስራኤል ወገን ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)