am_tn/ezk/39/17.md

1.9 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል ወፎች እና የዱር እንስሳት በጎግ ላይ ምን እንደሚያደርጉ መልዕክት ይሰጠዋል፡፡

የሰው ልጅ

"የሰብአዊ ፍጡር ልጅ" ወይም "የፍጥረታዊ ሰው ልጅ፡፡" እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ ብሎ የሚጠራው ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ እና ሀያል ነው፣ ሰዎች ግን እንዲህ አይደሉም፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ሟች የሆነ ሰው" ወይም "ሰብአዊ ፍጡር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ለመስዋዕት

ለመስዋዕት "ለግብዣ" ወይም "ለእርድ፡፡" ያህዌ ለወፎች እና ለእንስሳት በጣም ጥሩ ምግብ ይሰጣቸዋል ማለት እንጂ እርሱ ያመልካቸዋል ማለት አይደለም፡፡

እነርሱ አውራ በጎች፣ ጠቦቶች፣ ፍየሎች፣ እና ኮርማዎች ይሆናሉ

ያህዌ በምጸት እየተናገረ ነው፡፡ በተለመደው ሁኔታ ሰዎች ለእግዚአብሔር መስዋዕት ያቀርባሉ፡፡ እዚህ ስፍራ፣ እግዚአብሔር ሰዎችን ለእንስሳት እየሰዋ ነው፡፡ "እነርሱ ወንድ በጎች፣ ጠቦቶች፣ ፍየሎች፣ እና ወይፈኖች የሆኑ ይመስል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምጽት የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ሁሉም በባሳን የሰቡ ናቸው

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በባሳን ሲግጡ/የተሰማሩት ሁሉም ሰቡ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)