am_tn/ezk/39/14.md

1.9 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል በጎግ ላይ የሚደርስበትን መናገር ቀጥሏል፡፡

በምድሪቱ በሙሉ

"በእስራኤል ምድር በሙሉ"

ዘልቀው የተጓዙ፣ ነገር ግን ሞተው በድናቸው በሜዳ የወደቀ

ይህ የሚያመለክተው ወደ እስራኤል ምድር ሲገቡ ያህዌ የገደላቸውን የጎግ ወታደሮች በድን ነው

ስለዚህም እነርሱ ይቀብሯቸው ይሆናል

"ስለዚህም የተሰየሙ/የተቀጠሩ ወንዶች በድኖቹን ይቀብሩ ይሆናል"

ምድሪቱን ለማንጻት …ምድሪቱን ንጹህ ለማድረግ

በአይሁዶች ህግ፣ የሞተ አካል የሚነካውን ማናቸውንም ነገር ያረክሳል፤ ደግሞም "ያልነጻ" ያደርገዋል፡፡ እነዚህን አካሎች መቅበር የሚገለጸው ምድሪቱን እንደ ማንጻት ወይም ንጹህ እንደማድረግ ነው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰባተኛ ወር

ይህ "ሰባተኛ" ለሰባት ተከታታይ ቁጥር ነው፡፡ (ተከታታይ ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ማናቸውም የሰው አጥንት

ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ከበድኖች የሚቀረው ነው

መቃብር ቆፋሪዎች መጥተው እስኪቀብሩት ድረስ በዚህ ምልክት ያደርጋሉ

ሁለት ክፍል ሰዎች አሉ፡፡ የመጀመሪያዎቹ የበድኖቹን ስፍራ ይለያሉ፣ ሁለተኛው ቡድን በድኖቹን ይቀብራል፡፡

ሐሞን

የዚህ ስም ትርጉም "ታላቅ ሰራዊት" ማለት ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)