am_tn/ezk/39/12.md

2.0 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል በጎግ ላይ የሚደርስበትን መናገር ቀጥሏል፡፡

ሰባት ወራት

"7 ወራት፡፡" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

የእስራኤል ቤት

"ቤት" የሚለው በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች በዚህ ሁኔታ ለብዙ ዘመናት የያዕቆብ ትውልድ ለሆኑ እስራኤላውያን ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ይህ በሕዝቅኤል 3፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡ "እስራኤላውያን" ወይም "የእስራኤል ወገን ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ምድሪቱን ለማንጻት እነርሱን ይቀብሯቸዋል

በአይሁዶች ህግ፣ የሞተ አካል የሚነካውን ማናቸውንም ነገር ያረክሳል፤ ደግሞም "ያልነጻ" ያደርገዋል፡፡ እነዚህን አካሎች መቅበር የሚገለጸው ምድሪቱን እንደ ማንጻት ወይም ንጹህ እንደማድረግ ነው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱን መቅበር

"የጎግ ሰራዊትን ወታደሮች መቅበር"

ይህ የጌታ የያህዌ ትዕዛዝ ነው

ያህዌ ራሱን በስሙ የሚገልጸው/የሚምለው፤ የተናገረው እርግጠኛ መሆኑን ለማሳወቅ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ጌታ ያህዌ የተናገረው ይህንን ነው" ወይም "እኔ ጌታ ያህዌ የተናገርኩት ይህ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)