am_tn/ezk/39/09.md

1.5 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ መልዕክቱን ለጎግ ይነግረው ዘንድ ለሕዝቅኤል መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

ለመለኮስ እና እሳት ለማንደድ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ እስራኤላውያን ከመሳሪያዎች የሚያገኙትን እንጨት ለእሳት መለኮሻ ይጠቀሙበታል፡፡ "እሳት ለመለኮስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

ትንንሽ ጋሻዎች፣ ትላልቅ ጋሻዎች፣ ደጋኖች፣ ቀስቶች፣ ዱላዎች እና ጦሮች

እነዚህ ዝርዝሮች የዘመኑን አይነተኛ የጦር መሳሪያ አይነቶች ይጨምራል፡፡ በአጠቃላይ የጦር መሳሪያዎችን ሊወክል ይችላል፡፡

ዱላዎች

እንደ ጦር መሳሪያ የሚያገለግሉ የእንጨት ብትሮች

ለመቀማት መፈለግ.. ለመዝረፍ መፈለግ

እዚህ ስፍራ "መቀማት" እና "መዝረፍ" የሚሉት ተመሳሳይ ናቸው፡፡ ጎግ የእስራኤልን ሀብት ለመውሰድ ፈልጓል፣ ነገር ግን ያህዌ ጎግ ያንን ማድረግ እንዳይችል ከልክሎታል፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

ይዘርፋል… መዝረፍ ይፈልጋል

"ዝርፊያ" የሚለውን በሕዝቅኤል 23፡46 ላይ እንደ ተተረጎመው ይተርጉሙት፡፡