am_tn/ezk/39/07.md

1.5 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ መልዕክቱን ለጎግ ይነግረው ዘንድ ለሕዝቅኤል መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

ቅዱስ ስሜ በህዝቤ በእስራኤል መሃል እንዲታውቅ አደርጋሉ

እዚህ ስፍራ "ቅዱስ ስሜ" የሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ የሚያመለክተው የያህዌን ባህሪይ ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እኔ፣ ህዝቤ እስራኤል፤ እኔ ቅዱስ እንደሆነኩ እንዲያውቅ አደርጋለሁ" በሚው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

እነሆ!

ይህ አንባቢው ቀጥሎ ለሚሆነው ልዩ ትኩረት እንሰጥ ያደርገዋል፡፡ "ተመልከት!" ወይም "አድምጥ!" ወይም ቀጥሎ ለምነግርህ ትኩረት ስጥ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እየመጣ ነው… ይሆናል/ይፈጸማል

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ ደግሞም ይህ በእርግጥ እንደሚፈጸም ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ "በእርግጥ ይህ ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)