am_tn/ezk/39/04.md

2.9 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ መልዕክቱን ለጎግ ይነግረው ዘንድ ለሕዝቅኤል መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

ሰልፈኞችህ እና ወታደሮችህ

ይህ የሚያመለክተው ተመሳሳይ ሰዎችን ነው፡፡ በአንድ ሀረግ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ወታደሮችህ ሁሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

ለሰማይ ወፎች እና ለዱር አራዊት ምግብነት አሳልፌ እሰጥሃለሁ

ስጋ በል አሞሮች የሰዎችን በድን መብላታቸው የተገለጸው ያህዌ ለእነርሱ ምግብ እንደሰጣቸው ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የጌታ የያህዌ ትዕዛዝ ነው

ያህዌ ራሱን በስሙ የሚገልጸው/የሚምለው፤ የተናገረው እርግጠኛ መሆኑን ለማሳወቅ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ጌታ ያህዌ የተናገረው ይህንን ነው" ወይም "እኔ ጌታ ያህዌ የተናገርኩት ይህ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

በማጎግ ላይ እሳት እልካለሁ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ያህዌ በጎግ እና በሰራዊቱ ላይ ተፈጥሯዊውን እሳት ይልካል ወይም 2) "እሳት" ነገሩ ለሚያስከትለው ጥፋት ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ማጎግ

ይህ ምናላባት በአሁኗ ቱርክ ምድር ይኖሩ የነበሩ የጥንት ሰዎች ስም ነው፡፡ ማጎግ የሊድያ ጥንታዊ ህዝብ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 38፡2 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

እኔ ያህዌ እንደሆንኩ እወቁ

ያህዌ እርሱ ያህዌ እንደሆነ ሰዎች ያውቃሉ ሲል፣ የመጨረሻው ከፍተኛ ስልጣን እና ሀይል ያለው እውነተኛው አምላክ እርሱ ብቻ እንደሆነ ማወቅ እንደሚገባቸው እየተናገረ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል6፡7 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ብቸኛው እውነተኛ አምላክ እኔ ያህዌ እንደሆንኩ እወቁ" ወይም "እኔ ያህዌ የመጨረሻው ስልጣን እና ሀይል እንዳለኝ እወቁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)