am_tn/ezk/39/01.md

2.5 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ መልዕክቱን ለጎግ ይነግረው ዘንድ ለሕዝቅኤል ሰጠው፡፡

የሰው ልጅ

"የሰብአዊ ፍጡር ልጅ" ወይም "የፍጥረታዊ ሰው ልጅ፡፡" እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ ብሎ የሚጠራው ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ እና ሀያል ነው፣ ሰዎች ግን እንዲህ አይደሉም፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ሟች የሆነ ሰው" ወይም "ሰብአዊ ፍጡር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እነሆ!

ይህ አንባቢው ቀጥሎ ለሚሆነው ልዩ ትኩረት እንሰጥ ያደርገዋል፡፡ "ተመልከት!" ወይም "አድምጥ!" ወይም ቀጥሎ ለምነግርህ ትኩረት ስጥ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እኔ በአንተ ላይ ነኝ

"እኔ ጠላት ሆኜሃለሁ/ተነስቼብሃለሁ"

የሞሳህ እና የቶቤል አለቃ

አንዳንድ ዘመናዊ ቅጂዎች የዕብራይስጡን አገላለጽ "የሮህ፣ ሞሳህ እና ቶቤል አለቃ" ብለው ይተረጉሙታል፡፡ ይህ ለጎግ ሌላው መጠሪያ ነው፡፡ እነዚህ ስሞች በሕዝቅኤል 38፡2-3 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "የሞሳህ እና ቶቤል ዋና አለቃ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ እመልስሃለሁ፣ ደግሞም እነዳሃለሁ

እግዚአብሔር ጎግን እንደ እንስሳ እንደሚመራው ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ላይ አወጣሃለሁ

በተራሮች ላይ በመገኘቱ እግዚአብሔር ጎግን ወደ "ላይ" ወደ እስራኤል እንደሚያመጣው ይናገራል፡፡

ከግራ እጅህ ደጋንህን እመታለሁ፤ ከቀኝ እጅህም ቀስትህ እንዲወድቅ አደርጋለሁ

የጎግን ደጋን መምታት እና ቀስቶችን ከእጁ ማስጣል የተገለጸው እግዚአብሔር የጎግ ሰራዊት ሀይል እንደሚያጠፋው ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)