am_tn/ezk/38/21.md

4.3 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ስለ ጎግ መልዕክቱን ለሕዝቅኤል መስጠቱን ይቀጥላል፡፡ ስለ ጎግ ህዝብ አንድ ሰው እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእርሱ ላይ ሰይፍ እጠራለሁ

እዚህ ስፍራ "ሰይፍ" የሚለው ቃል ሰዎችን ለመግደል ሰይፍ ለሚጠቀሙ ወታደሮች ሜቴኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ወታደሮች እርሱን እንዲያጠቁ አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በሁሉም ተራሮቼ ላይ

ይህ የእስራኤልን ምድር ያመለክታል፡፡ "በሁሉም የእስራኤል ተራሮች ላይ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የእያንዳንዱ ሰው ሰይፍ በወንድሙ ላይ ይሆናል

እዚህ ስፍራ "ሰይፍ" ለውጊያ ሰይፉን ለሚጠቀምበት ሰው ሜቴኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ወታደሮቹ በሙሉ እርስ በእርሳቸው ይዋጋሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ወንድሙ

"አብሮት የተሰለፈው ወታደር"

በመቅሰፍት እና በደም እፈርድበታለሁ

እዚህ ስፍራ "ደም" ለጉዳት እና ሞት ሜቴኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "በህመም እና ሰራዊት እንዲገድለው በመላክ እፈርድበታለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ጎርፍ፣ ከባድ በረዶ እና የሚነድ ድኝ በላዩ አፈሳለሁ

የዐረፍተ ነገሩን ቅደም ተከተል መቀየር ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡ የዝናብ ጎርፍ እና ከባድ በረዶ እንዲሁም ድኝ በላዩ አፈሳለሁ"

ከባድ በረዶ

ከሰማይ የሚወርድ በረዶ

ታላቅነቴን እና ቅዱስነቴን አሳያለሁ

"ታላቅነት" እና "ቅዱስነት" የሚሉት ረቂቅ ስሞች በቅጽል መልክ ሊጻፉ ይችላሉ፡፡ "ታላቅ እና ቅዱስ መሆኔን አሳያለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

በብዙ ህዝቦች ዐይኖች ፊት ራሴን አሳውቃለሁ

እዚህ ስፍራ "ዐይኖች" የሚለው የሚያመለክተው ለመረዳት ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ የሆነውን እይታን ነው፡፡ "ብዙ አገሮች እኔ ማን እንደሆንኩ እንዲያውቁ አደርጋለሁ፡፡ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ያህዌ እንደሆንኩ እወቁ

ያህዌ እርሱ ያህዌ እንደሆነ ሰዎች ያውቃሉ ሲል፣ የመጨረሻው ከፍተኛ ስልጣን እና ሀይል ያለው እውነተኛው አምላክ እርሱ ብቻ እንደሆነ ማወቅ እንደሚገባቸው እየተናገረ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል6፡7 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ብቸኛው እውነተኛ አምላክ እኔ ያህዌ እንደሆንኩ እወቁ" ወይም "እኔ ያህዌ የመጨረሻው ስልጣን እና ሀይል እንዳለኝ እወቁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)