am_tn/ezk/38/19.md

1.3 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ስለ ጎግ መልዕክቱን ለሕዝቅኤል መስጠቱን ይቀጥላል፡፡

በእኔ ቅናት

እዚህ ስፍራ "ቅናት" የሚለው የሚያመለክተው ክብሩን ከጎግ ጥቃት ለመጠበቅ ያለውን ፍላጎት ነው፡፡

በቁጣዬ እሳት

የያህዌ ቁጣ ታላቅነት የተገለጸው እንደ እሳት የሚፋጅ ተደርጎ ነው፡፡ "ቁጣዬ ጠንካራ በመሆኑ ምክንያት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በፊቴ ይንቀጠቀጣሉ

የሚንቀጠቀጡት ስለ ፈሩ ነው፡፡ ይህ ይበልጥ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ "በፊቴ በፍርሃት ይንቀጠቀጣሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ተራሮች ወደ ታች ይወረወራሉ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ያህዌ ተራሮች እንዲወድቁ ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)