am_tn/ezk/38/17.md

2.5 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል ለጎግ መናገር ያለበትን መናገሩን ይቀጥላል፡፡

በእነርሱ ላይ ያመጣሁህ/ያስነሳሁህ… አንተ አይደለህምን?

ያህዌ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው ጎግን ወደ እስራኤል ምድር ያመጣው እርሱ መሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "በእነርሱ ላይ ያመጣሁህ… አንተ ነህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ የተናገርኩህ

"ያ እኔ የተናገርኩት"

በቀደሙት ቀናት

"ባለፈው ዘመን" ወይም "ከረጅም ጊዜ አስቀድሞ"

በአገልጋዬ እጅ

እዚህ ስፍራ "እጀ" የሚያመለክተው እነዚህ ነቢያት የያህዌን መልዕክት የመጻፋቸውን እውነታ ነው፡፡ "በአገልጋዮቼ አማካይነት" ወይም "በአገልጋዮቼ በኩል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በእነርሱ ላይ/እነርሱን በመቃወም

"በእስራኤል ህዝብ ላይ"

ይህ የጌታ የያህዌ ትዕዛዝ ነው

ያህዌ ራሱን በስሙ የሚገልጸው/የሚምለው፤ የተናገረው እርግጠኛ መሆኑን ለማሳወቅ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ጌታ ያህዌ የተናገረው ይህንን ነው" ወይም "እኔ ጌታ ያህዌ የተናገርኩት ይህ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ቁጣዬ በንዴት ከፍ ይላል

እዚህ ስፍራ "ከፍ ይላል" ማለት "ይነሳል" ማለት ሲሆን ቁጣው እንደሚጨምር ይገልጻል፡፡ "ቁጣ" እና "ንዴት" የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ነገርን ሲገልጹ፣ በአንድነት ቁጣው ምን ያህል ጠንካራ እንደሚሆን ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ "ቁጣዬ እጅግ ይጨምራል" ወይም "በእናንተ ላይ እጅግ እቆጣለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ጥንድ ትርጉም የሚሉትን ይመልከቱ)