am_tn/ezk/38/14.md

2.0 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል ለጎግ መናገር ያለበትን ይነግረዋል፡፡

የሰው ልጅ

"የሰብአዊ ፍጡር ልጅ" ወይም "የፍጥረታዊ ሰው ልጅ፡፡" እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ ብሎ የሚጠራው ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ እና ሀያል ነው፣ ሰዎች ግን እንዲህ አይደሉም፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ሟች የሆነ ሰው" ወይም "ሰብአዊ ፍጡር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

በዚያን ቀን… ስለ እነርሱ ታውቃለህ?

ያህዌ ይህንን ጥያቄ የሚያነሳው ጎግ በእስራኤል ውስጥ ስለሚኖሩ ሰዎች በእርግጥ መስማቱን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "በዚያን ቀን፣ ህዝቤ እስራኤል ተጠብቀው ሲኖሩ ስለ እነርሱ ትሰማለህ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ምድሪቱን እንደ ሸፈነ ደመና

የዚህ ተነጻጻሪ ዘይቤ ትርጉም ሰራዊቱ መላዋን ምድር እስኪሸፍን ድረስ ብዙ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 38፡9 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በኋለኞቹ ቀናት

ይህ የሚያመለክተው ዓለም ከመጥፏትዋ በፊት ያለውን ጊዜ ነው፡፡ "በመጨረሻው ቀን" ወይም "በዓለም መጨረሻ"

በኋልኞቹ ቀናት… በዐይኖቻቸው ፊት ቅዱስ እንድሆን

መላው ህዝብ ያህዌ በጎግ ላይ ያደረገውን ሲመለከቱ እርሱ ቅዱስ እንደሆነ ያውቃሉ

ያውቁኛል

"እኔ ማን እንደሆንኩ ያውቃሉ"