am_tn/ezk/38/13.md

1.5 KiB

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ለጎግ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

ሳባ

ይህ በሕዝቅኤል 27፡22 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

ድዳን

ይህ በሕዝቅኤል 25፡13 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

የመጣኸው ለመዝረፍ ነውን? ብዙ ዝርፊያ ለመሰብሰብ… ሰራዊትህን አሰባስበሃል?

እነዚህ ሁለት ጥያቄዎች ጎግ እስራኤልን ያለ ምክንያት ለማጥቃት በመነሳቱ እርሱን ለመክሰስ የቀረቡ ናቸው፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ለንጥቂያ፣ ወርቅና ብር ለመውሰድ፣ ከብቶቻቸውን እና ንብረታቸውን፣ እንደዚሁም ብዙ ሀብት ለመዝረፍ ሰራዊትህን መሰብሰብህ ትክክል አይደለም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ከብቶቻቸውን እና ንብረታቸውን… ብዙ ንብረት በዝርፊያ ለመውሰድ

እነዚህ ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ እናም በአንድ ሀረግ ሊጠቃለሉ ይችላሉ፡፡ "ከብቶቻቸውን ለመንጠቅ እና ከፍ ያለ ዋጋ ያላቸውን ሀብቶቻቸውን ለመዝረፍ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)