am_tn/ezk/38/01.md

2.4 KiB

የያህዌ ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢዩ ወይም ለህዝቡ የተናገረውን ነገር ለማስተዋወቅ የዋለ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ ይህንን መልዕክት ነናገረ" ወይም "ያህዌ እነዚህን ቃላት ተናገረ/ያህዌ እንዲህ አለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ፊትህ ወደ ጎግ መልስ፣ የማጎግ ምድር ፣ ዋናው ልዑል/አለቃ...ቶቤል

በዚያ ያሉ ሰዎችን ትኩር ብሎ መመልከት ይህ ጎግን እና ማጎግን ለመቅጣት በምልክትነት የተሰጠ ትዕዛዝ ነው፡፡ ተመሳሳዩ ሀረግ በሕዝቅኤል 4፡3 ላይ እንዴት አንደተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ዋና አለቃውን… ቶቤል፣ የማጎግን ምድር እና ጎግን ትኩር ብለህ ተመልከት" ወይም "ወደ ዋና አለቃው ጎግ፣…ይቀጡ ዘንድ ወደ ቶቤል፣ እና ወደ ማጎግ ምድር ትኩር ብለህ ተመልከት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምልክታዊ/ትዕንርታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

ፊትህን አድርግ

እዚህ ስፍራ "ፊት" ለትኩረት ወይም ለመመልከት ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ፊትህን አድርግ" የሚለው የሚወክለው ትኩር ብሎ መመልከትን ነው፡፡ "ትኩር ብለህ ተመልከት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ጎግ፣ የማጎግ ምድር

ጎግ በሚገዛበት አካባቢ ማጎግ ምድር እንደሆነ በውስጠ ታዋቂነት ተጠቁሟል፡፡ "በማጎግ ምድር የሚገዛው ጎግ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ጎግ

ይህ በማጎግ ምድር የሚገዛ መሪ ወይም ንጉሥ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)