am_tn/ezk/35/14.md

3.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ይህ ሕዝቅኤል ለሴይር ተራራ የሚናገረውን መልዕክት ይቀጥላል፡፡ መልዕክቱ ለመላው የኤዶም ሰዎች ነው፡፡

ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል

ይህ በአንደኛ መደብ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እኔ፣ ጌታ ያህዌ የምናገረው ይህ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

አንተን ምድረ በዳ/ጠፍ ምድር አደርግሃለሁ

እዚህ ስፍራ "አንተ" የሚለው የሴይር ተራሮችን ነው፣ ነገር ግን መልዕክቱ ለኤዶም ሰዎች ነው፡፡ "ጠፍ/ሰው የማይኖርበት ምድር" የሚለው ረቂቅ ስም በቅጽል መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የአንተ ህዝብ ባደረገው ነገር ምክንያት አንተን ሰው የማይኖርበት ምድረ በዳ አደርግሃለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

መላዋ መሬት ሀሴት ታደርጋለች

እዚህ ስፍራ "መሬት" የሚለው ቃል የሚወክለው የምድር ሰዎችን ነው፡፡ "መላው" የሚለው ቃል በሴይር ተራሮች አቅራቢያ ብቻ የሚኖሩ ሰዎችን የሚያመለክት ማጠቃለያ ነው፡፡ "እኔ የአንተን ደስታ መደምሰሴን የሚያውቁ ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እስራኤል ሰው የማይኖርባት በመሆኗ ምክንያት በህዝቧ ርስት አንተ ሀሴት በምታደርግበት ጊዜ

ይህ የሚገልጸው ያህዌ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጎ የሰጣቸውን ምድር ነው፡፡ "የእስራኤልን ምድር ሰው የማይኖርበት ባደረግሁ ጊዜ አንተ ሀሴት እንዳደረግህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በአንተ ላይም እንደዚያው አደርጋለሁ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "እኔ ምድርህን ሰው የማይኖርበት አደርጋለሁ" ወይም 2) "የአንተ ምድር ሰው የማይኖርበት በሚሆንበት ጊዜ እኔ ሀሴት አደርጋለሁ" ወይም 3) "አንተ ጠፍ/ሰው የማይኖርበት ስፍራ በመሆንህ ምክንያት ሌሎች ደስ እንዲላቸው አደርጋለሁ"

የሴይር ተራራ እና መላው ኤዶም፣ ሰው የማይኖርበት ትሆናላችሁ

ያህዌ ለህዝቅኤል ለሴይር ተራራ መስማት እንደሚችል አድርጎ መናገሩን እንዲቀጥል ይነግረዋል፡፡ መልዕክቱ ለኤዶም ህዝብ ሁሉ ነው፡፡ "የሴይር ተራራ እና መላውን ኤዶም ሰው የማይኖርባቸው አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚያ… እነርሱ ያውቃሉ

"እነርሱ" የሚለው ቃል ሊያመለክት የሚችለው 1) "የመሬት ሰዎች" ወይም 2) "የእስራኤል እና የይሁዳ ሰዎች"