am_tn/ezk/35/12.md

1.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ይህ ሕዝቅኤል ለሴይር ተራራ የሚናገረውን መልዕክት ይቀጥላል፡፡ መልዕክቱ ለመላው የኤዶም ሰዎች ነው፡፡

በእስራኤል ተራሮች ላይ

እዚህ ስፍራ "ተራሮች" የሚለው የሚወክለው መላውን የእስራኤል ምድር ነው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ተደምስሰዋል

ይህ ሀረግ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በፍርስራሾች ስር ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ እንድንበላቸው ለእኛ ተላልፈው ተሰጥተዋል

የሴይር ተራሮች ህዝብ የእስራኤልን ምድር ወስደው ለራሳቸው መጠቀሚያ ማድረጋቸው የተገለጸው የዱር እንስሳት እንደሆኑ እና የእስራኤል ተራሮችን እንደሚበሉ ተደርጎ ነው፡፡ "እነርሱ በዚህ ያሉት እኛ እንደንበላቸው ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)