am_tn/ezk/35/10.md

1.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ይህ ሕዝቅኤል ለሴይር ተራራ የሚናገረውን መልዕክት ይቀጥላል፡፡ መልዕክቱ ለመላው የኤዶም ሰዎች ነው፡፡

አንተ እንዲህ ብለሃል

"አንተ" የሚለው ቃል የሴይር ተራሮችን ያመለክታል፡፡ ሕዝቅኤል ለተራራው የሚናገረው ተራራው እንደሚሰማው አድርጎ ነው፡፡ መልዕክቱ ለኤዶም ሰዎች ነው፡፡ "ህዝቦችህ እንዲህ ብለዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እነዚህ ሁለት ምድሮች

"የእስራኤል እና ይሁዳ ምድሮች"

የእኔ ይሆናሉ

"የእኔ" የሚለው ቃል በብዙ ቁጥር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የእኛ ይሆናሉ"

እኛ

"እኛ" የሚለው ቃል የኤዶምን ሰዎች ያመለክታል፡፡

ያህዌ ከእነርሱ ጋር በነበረበት ጊዜ እንኳን

ያህዌ እስራኤልን እና ይሁዳን ይጠብቅ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡ "ነገር ግን ያህዌ እስራኤልን እና ይሁዳን እየጠበቀ በዚያ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ቁጣችሁ እና ቅናታችሁ አደርግባችኋለሁ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "በቁጣችሁ እና ቅናታችሁ ምክንያት እቀጣችኋለሁ" ወይም 2) "በቁጣና ቅናት በእስራኤል ህዝብ ላይ እንዳደረጋችሁት ልክ እንደዚያው እኔም በእናንተ ላይ በቁጣ እና ቅናት አደርግባችኋለሁ"