am_tn/ezk/35/07.md

2.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ይህ ሕዝቅኤል ለሴይር ተራራ የሚናገረውን መልዕክት ይቀጥላል፡፡ መልዕክቱ ለመላው የኤዶም ሰዎች ነው፡፡

ከእርሱ በዚያ የሚያልፈውንመ ቆርጬ ስጥል እና እንደ ገና ስመለስ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "ቆርጦ መጣል" የሚለው ዘይቤያዊ አነጋገር ሲሆን ማጥፋት/መደምሰስ ማለት ነው፡፡ "ወደ እርሱ የሚገቡትንም ሆነ የሚወጡትን ሁሉ አጠፋለሁ ወይም 2) "ቆርጦ መጣል" አንድ ሰው አንድ ነገር እንዳያደርግ ማስቆም ለሚለው ዘይቤያዊ አገላለጽ ነው፡፡ "ሰዎች ወደ እርሱ እንዳይገቡና እንዳይወጡ/እንዳይመላለሱ አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በሰይፍ የተገደሉ

እዚህ ስፍራ "ሰይፍ" የሚለው የሚወክለው በጦርነት የተዋጓቸውን ጠላቶቻቸውን ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 31፡17 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ጠላት በሰይፍ የገደላቸው" ወይም "በጦርነት የሞቱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ እና ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

ለአንዴው ጠፍ የሆነ

"እስከ ወዲያኛው ምድረ በዳ የሆነ፡፡" ይህ ጥፋቱን ትኩረት ሰጥቶ ለማጋነን የተነገረ ሊሆን ይችላል፡፡ "ከእንግዲህ ሰዎች በእናንተ ከተሞች ውስጥ አይኖሩም" (አድራጊ ወይም ተደራጊ እና ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት ሚሉትን ይመልከቱ)

ነገር ግን እናነተ ታውቃላችሁ

"እናንተ" የሚለው ብዙ ቁጥር ነው፡፡ እግዚአብሔር በአንድ ተራራ ለሚኖሩ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በሴይር ተራሮች ለሚኖሩ ሰዎች እየተናገረ ነው፡፡ (አንተ/አንቺ የሚለው ነጠላ ቁጥር ተውላጠ ስም መልኮች)