am_tn/ezk/35/04.md

4.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ሕዝቅኤል ለሴይር ተራራ የሚናገረውን መልዕክት ይቀጥላል፡፡ መልዕክቱ ለመላው የኤዶም ሰዎች ነው፡፡

እኔ ያህዌ እንደሆንኩ እወቁ

ያህዌ እርሱ ያህዌ እንደሆነ ሰዎች ያውቃሉ ሲል፣ የመጨረሻው ከፍተኛ ስልጣን እና ሀይል ያለው እውነተኛው አምላክ እርሱ ብቻ እንደሆነ ማወቅ እንደሚገባቸው እየተናገረ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል6፡7 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ብቸኛው እውነተኛ አምላክ እኔ ያህዌ እንደሆንኩ እወቁ" ወይም "እኔ ያህዌ የመጨረሻው ስልጣን እና ሀይል እንዳለኝ እወቁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ለሰይፍ እጅ አሳልፈህ ሰጠሃቸው

የዚህ ዘይቤ ትረጉም ሊሆኑ የሚችሉት 1) "በሰይፍ ለሚገድሏቸው ጠላቶቻቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው" ወይም 2) "በሰይፍ ገደልካቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በጉዳታቸው ጊዜ

"በጥፋት ጊዜ"

በህያውነቴ

"እኔ ህያው እንደሆንኩ፡፡" ያህዌ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው ቀጥሎ የሚናገረው በእርግጥ እውነት መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ ይህ የከበረ ቃል መግቢያ መንገድ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "በክብሬ እምላለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የጌታ የያህዌ ትዕዛዝ ነው

ያህዌ ራሱን በስሙ የሚገልጸው/የሚምለው፤ የተናገረው እርግጠኛ መሆኑን ለማሳወቅ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ጌታ ያህዌ የተናገረው ይህንን ነው" ወይም "እኔ ጌታ ያህዌ የተናገርኩት ይህ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ለደም ማፍሰስ አዘጋጃችኋለሁ

እዚህ ስፍራ "ደም ማፍሰስ" መግደል ለሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ለጠላቶቻችሁ ብዙዎቻችሁን መግደልን ቀላል አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ደም ማፍሰስ ይከተላችኋል

እዚህ ስፍራ "ደም መፍሰስ" መግደል ለሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ ያህዌ ስለ ደም ማፍሰስ የሚናገረው ሊያባርራቸው እንደሚችል ሰው አድርጎ ነው፡፡ "ጠላቶቻችሁ ቁልቁል አሳደው ይገደሏችኋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ደም ማፍሰስን አልጠላችሁምና

እዚህ ስፍራ "ደም መፍሰስ" መግደል ለሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ጠላት የእስራኤልን ህዝብ በጭካኔ ሲገድል ይህን ድርጊት አልጠላችሁምና" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)