am_tn/ezk/35/01.md

4.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል ትንቢት እንዲናገር ይነግረዋል፡፡ ሕዝቅኤል ለሴይር ተራራ መናገር ይኖርበታል፣ ነገር ግን መልዕክቱ ለመላው የኤዶም ህዝብ ነው፡፡

የያህዌ ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢዩ ወይም ለህዝቡ የተናገረውን ነገር ለማስተዋወቅ የዋለ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ ይህንን መልዕክት ነናገረ" ወይም "ያህዌ እነዚህን ቃላት ተናገረ/ያህዌ እንዲህ አለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው ልጅ

"የሰብአዊ ፍጡር ልጅ" ወይም "የፍጥረታዊ ሰው ልጅ፡፡" እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ ብሎ የሚጠራው ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ እና ሀያል ነው፣ ሰዎች ግን እንዲህ አይደሉም፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ሟች የሆነ ሰው" ወይም "ሰብአዊ ፍጡር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ፊትህን ወደ ሴይር ተራራ መልስ

የሴይር ተራራ ሩቅ ነው፣ ስለዚህ ሕዝቅኤል ሊመለከተው አይችልም፤ ነገር ግን ያህዌ በዚያ ላሉ ሰዎች ቅጣት እንዲደርስባቸው እንደ ምልክት ወደዚያ አቅጣጫ እንዲያይ ያዘዋል፡፡ ተመሳሳይ የሆነው ሀረግ በሕዝቅኤል 6፡2 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ወደ ሴይር ተራራ ዞረህ ትኩር ብለህ ተመልከት" ወይም "በዚያ የሚኖሩ ጥፋት ይደርስባቸው ዘንድ ወደ ሴይር ትኩር ብለህ ተመልከት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትምዕርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

የሴይር ተራራ እና በእርሱ ላይ የተነገረ ትንቢት

"የሴይር ተራራ፡፡" ያህዌ ለሕዝቅኤል የሚሰማ ይመስል ለሴይር ተራራ እንዲናገር ይናገረዋል፡፡ መልዕክቱ ለመላው የኤዶም ህዝብ ነው፡፡ "የሴይር ተራራ እና የኤዶም ሰዎች ከፈጸሙት ነገር የተነሳ በእርሱ ላይ የተነገረ ትንቢት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእርሱ

"ለተራራው" ወይም "ለኤዶም ሰዎች"

የሴይር ተራራ ሆይ እነሆ! እኔ በአንተ ላይ ነኝ፣ በእጄ እመታሃለሁ ደግሞም ጠፍ እና ምድረበዳ አደርግሃለሁ

ያህዌ ለሕዝቅኤል ለሴይር ተራራ ልክ እንደሚሰማው አድርጎ እንዲናገር ያዘዋል፡፡ መልዕክቱ ለመላው የኤዶም ህዝብ ነው፡፡ "የሴይር ተራራ ሆይ ስማ፣ በእጄ እመታሃለሁ ደግሞም የአንተ ህዝብ ካደረገው የተነሳ ጠፍ እና ምድረበዳ አደርግሃለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ!

እዚህ ስፍራ "እነሆ!" የሚለው ቃል ቀጥሎ ለሚሆነው ትኩረት ይጨምራል፡፡ "አድምጡ!" ወይም "በእርግጥ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እኔ በእናንተ ላይ ነኝ

"እኔ ጠላታችሁ ነኝ" ወይም "እኔ እቃመዋችኋለሁ"

በእጄ እመታችኋለሁ

እዚህ ስፍራ "እጅ" ሀይልን ይወክላል፡፡ "እናንተን ለመምታት ሀይሌን እጠቀማለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ሰው የማይኖርበት ምድር/ጠፍ አደርግሃለሁ

"ጠፍ/ምድረበዳ" የሚለው ረቂቅ ስም በቅጽል ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ምድረ በዳ አደርግሃለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)