am_tn/ezk/34/30.md

1.4 KiB

እኔ፣ ያህዌ አምላካቸው እኔ ከእነርሱ ጋር ነኝ

እዚህ ስፍራ "እኔ…ከእነርሱ ጋር ነኝ" የሚለው ያህዌ ይረዳቸዋል ለሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "እኔ፣ ያህዌ አምላካቸው፣ እኔ እረዳቸዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከእነርሱ ጋር፡፡ እነርሱ የእኔ ህዝብ ናቸው

ይህ በአንድ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እነርሱ የእኔ ህዝብ ናቸው፣ እኔ ከእነርሱ ጋር እሆናለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የእስራኤል ቤት

እዚህ ስፍራ "ቤት" የሚወክለው ሰዎችን ነው፡፡ "የእስራኤል ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ለእናንተ ለበጎቼ፣ ለመሰማሪያ መንጋዎቼ

ይህ የእስራኤል ህዝብ ለእርሱ የበጎች መንጋ እንደሆኑ እና ያህዌ እረኛቸው እንደሆነ ይገልጻል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)