am_tn/ezk/34/25.md

3.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል ስለ እስራኤል ሰዎች መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ስለ እስራኤል ሰዎች እንደ በጎች መንጋ አድርጎ መግለጹን ቀጥሏል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሰላም ቃል ኪዳን

"ሰላም የሚያመጣ ቃል ኪዳን"

ክፉ የዱር እንስሳት

እነዚህ በጎችን እና ፍየሎችን መግደል የሚችሉ የዱር እንስሳት ናቸው፡፡

እኔ በእነርሱ እና በኮረብቶቼ ዙሪያ በሚገኙ ስፍራዎች በረከትንም ጭምር አመጣለሁ

አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ይህንን "እነርሱን እና በኮረብቶቼ ዙሪያ የሚገኙ ስፍራዎችን ወደ በረከት እለውጣቸዋለሁ" ብለው ይተረጉማሉ፡፡

የእኔ ኮረብታ

ይህ የሚያመለክተው የጽዮንን ተራራ ነው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ዝናብን እልካለሁ

"እንዲዘንብ አደርጋለሁ"

በጊዜው

"በትክክለኛው ጊዜ"

እነዚህም የበረከት ዝናብ ይሆናሉ

"ይህ ዝናብ በረከት ይሆናል"

ምድር ፍሬዋን ትሰጣለች

"ምድር የሚበላ ታበቅላለች" ወይም "ምግብ በምድር ይበቅላል"

አስተማማኝ ይሆናል

"ደህና ይሆናል"

እኔ ያህዌ እንደሆንኩ እወቁ

ያህዌ እርሱ ያህዌ እንደሆነ ሰዎች ያውቃሉ ሲል፣ የመጨረሻው ከፍተኛ ስልጣን እና ሀይል ያለው እውነተኛው አምላክ እርሱ ብቻ እንደሆነ ማወቅ እንደሚገባቸው እየተናገረ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል6፡7 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ብቸኛው እውነተኛ አምላክ እኔ ያህዌ እንደሆንኩ እወቁ" ወይም "እኔ ያህዌ የመጨረሻው ስልጣን እና ሀይል እንዳለኝ እወቁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የቀንበራቸውን እስራት ስሰብር

ባርነት የተገለጸው እንደ አንዳንድ እንስሳት ሰዎች ላይ ቀንበር እንደሚጫንባቸው ተደርጎ ነው፡፡ "ከባርነት ነጻ ሳወጣቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በባርነት ከያዝዋቸው እጅ

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚወክለው ሀይልን ወይም መቆጣጠርን ነው፡፡ "ባሪያ አድርገው ከተቆጣጠሯቸው እጅ" ወይም "እነርሱን ባሪያዎች ካደረጓቸው እጅ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)