am_tn/ezk/34/22.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ስለ እስራኤል ሰዎች እንደ በጎች መንጋ፤ ስለ ራሱ የእነርሱ እረኛ እንደሆነ መግለጹን ቀጥሏል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከእንግዲህ አይበዘበዙም

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ማንም እንዲበዘብዛቸው አልፈቅድም" ወይም "ማንም እንዲሰርቃቸው አልፈቅድም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚህ በኋላ ዘረፋ አይሆንም

"ከዚህ በኋላ የሚሰረቅ ነገር አይኖርም፡፡" እረኞቹ እና የዱር እንስሳቱ ከያህዌ መንጋ በጎቹን እና ፍየሎቹን ይሰርቁ ነበር፡፡

በላያቸው አንድ እረኛ አስቀምጣለሁሁ

"በላያቸው አስቀምጣለሁ" የሚለው ሀረግ ፈሊጥ ሲሆን ትርጉሙ አንድ ሰው ሌላውን እንዲያስተዳድር ማድረግ ማለት ነው፡፡ "አንድ እረኛ በበጎቼ እና ፍየሎቼ ላይ እሾማለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አገልጋዬ ዳዊት

እዚህ ስፍራ "ዳዊት" የተጠቀሰው ለዳዊት ትውልድ ነው፡፡ "የአገልጋዬ የዳዊት ትውልድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ እረኛ ይሆናቸዋል

በእስራኤል ህዝብ ላይ ንጉሥ የሚሆነው የዳዊት ትውልድ የተገለጸው የእነርሱ እረኛ እንደሚሆን ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእነርሱ መሃል ልዑል/ገዢ ይሆናል

"ገዢያቸው ይሆናል"