am_tn/ezk/34/17.md

2.0 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ በሕዝቅኤል በኩል ለእስራኤል መሪዎች መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ መልዕክቱን ለሕዝቅኤል መስጠቱን ቀጥሏል፡፡ አሁን መልዕክቱ ለእስራኤል ህዝብ ነው፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ስለ እስራኤል ሰዎች እንደ በጎች መንጋ፤ ስለ ራሱ የእነርሱ እረኛ እንደሆነ ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል

ይህ በአንደኛ መደብ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እኔ፣ ጌታ ያህዌ የምናገረው ይህ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ፣ እኔ

"ትኩረት ስጡ፣ ምክንያቱም እኔ የምናገረው እውነተኛም ጠቃሚም ነውና"

እኔ በበጎች እና በበጎች መሃል ዳኛ እሆናለሁ

"እኔ በአንደኛው በግ እና በሌላኛው መሃል ዳኝነት እሰጣለሁ"

አውራ በጎች እና ወንድ ፍየሎች

ወንድ በጎች እና ፍየሎች ብዙውን ጊዜ በመንጋው ውስጥ ጠንካሮቹ ናቸው፤ ደግሞም የሚፈልጉትን በመንጋው ውስጥ ከሚገኙት እንስሳት ያገኛሉ፡፡

ይህ … በቂ አይደለምን

እግዚአብሔር እነዚህን ጥያቄዎች የተጠቀመው፣ በመንጋው ውስጥ የሚገኙትን፤ ለደካሞቹ በማያዝኑ ጠንካራ እንስሳት የተገለጹትን የእስራኤል መሪዎችን ለመገሰጽ ነው፡፡ ይህንን በዩዲቢ እንደሚገኘው በዐረፍተ ነገር መልክ መተረጎም ይቻላል፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)