am_tn/ezk/34/14.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ በሕዝቅኤል በኩል ለእስራኤል መሪዎች መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ስለ እስራኤል ሰዎች እንደ በጎች መንጋ አድርጎ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ እዚህ ስፍራ ስለ ራሱ የእነርሱ እረኛ እንደሆነ እና እንደሚንከባከባቸው ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የግጦሽ ስፍራቸው

"ሊሚመገቡ/ሊግጡ የሚችሉበት ስፍራ"

ሰፊ መሰማሪያ

"ብዙ ሳር እና ተክል የሚገኝበት እንስሳት ግጦሽ መሬት"

መጋጥ

እንስሳት ሳር እና ሌሎች ተክሎች ማግኘታቸው

እኔ ራሴ

"እኔ ራሴ" የሚለው ትኩረት ይጨምራል፡፡ እግዚአብሔር ይህን የሚያደርገው እረኞች ያንን ባለማድረጋቸው ነው፡፡ (ደጋጋሚ ተውላጠ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

እረኞች… ይሆን

"ይመግቧቸው እና ይንከባከቧቸው…ይሆን

እንዲጋደሙ ያደርጉ ይሆን

"እንዲያርፉ ይተዋቸው ይሆን"

የጠፉት

"በጎቹ ወይም ፍየሎች" የሚሉት ቃላት በእዚህ ሀረግ ተዘለዋል/ተትተዋል፤ ሆኖም ግንዛቤ እንደሚያገኑ ይታሰባል፡፡ "የጠፉት በጎች ወይም ፍየሎች" (የተዘለለ/የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)

የተጣሉትን ጠግኑ

"ሌሎች ያባረሯቸውን/ያስወጧቸውን መልሷቸው"

የተሰበሩትን በጎች ጠግኑ

"የተሰበረውን በግ አጥንቱን በጨርቅ ጠቅልሉ" ወይም "የማናቸውንም በግ ቁስል ዙሪያውን በጨርቅ ጠቅልሉ"

የሰባውን እና ጠንካራውን/ጤናማውን

"በግ" የሚለው ቃል በውስጠ ታዋቂነት አለ፡፡ "የሰባው እና ጠንካራው/ጤናማውን በግ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተዘለለ/የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)