am_tn/ezk/34/09.md

2.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ በሕዝቅኤል በኩል ለእስራኤል መሪዎች መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ስለ እስራኤል ሰዎች እንደ በጎች መንጋ፣ የእስራኤል መሪዎችን ደግሞ ለመንጋው ግድ እንደማይላቸው እረኞች አድርጎ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የያህዌን ቃል ስሙ

"የያህዌን መልዕክት አድምጡ፡፡" ይህ ከያህዌ ልዩ መልዕክት ለማስተዋወቅ የዋለ ፈሊጥ ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል

ይህ በአንደኛ መደብ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እኔ፣ ጌታ ያህዌ እንዲህ እላለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ!

እዚህ ስፍራ "እነሆ!" የሚለው ቃል ቀጥሎ ለሚሆነው ነገር ትኩረት ይሰጣል፡፡ "በእርግጥ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እኔ በእረኞች ላይ ተነስቻለሁ

"እኔ እረኞችን እቃወማለሁ"

በጎቼን ከእጃቸው እጠይቃለሁ

"ከእጃቸው…መጠየቅ" የሚለው ሀረግ አንድን ሰው ለአንድ ነገር ተጠያቂ ወይም በሀላፊነት ተጠያቂ ማድረግ ማለት ነው፡፡ "በመንጋዬ ላይ ለደረሰው ከፉ ነገር ሁሉ ተጠያቂ አደርጌ እይዛቸዋለሁ" ወይም "በመንጋዬ ላይ እንዲደርስ ላደረጉት ክፉ ነገር ሁሉ እቀጣቸዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መንጋውን ከመጠበቅ ሃላፊነት ላይ እደመስሳቸዋለሁ

"ከእንግዲህ መንጋውን እንዲጠብቁ አልፈቀድላቸውም" ወይም "ከዚህ በኋላ የመንጋው ጠባቂ እንዲሆኑ አልተዋቸውም/አላደርግም"

ራሳቸውን ተንከባከቡ/ጠበቁ

"ራሳቸውን መገቡ ወይም ለራሳቸው እንክብካቤ አደረጉ"

ከእነርሱ አፍ

እዚህ ስፍራ "አፍ" የሚወክለው መብላትን ነው፡፡ "ከእንግዲህ አይበሏቸውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

መንጋዎቼ ከእንግዲህ ለእነርሱ ምግብ አይሆኑም

"እረኞቹ ከእንግዲህ የመንጋዬን በጎች እና ፍየሎች አይበሉም"