am_tn/ezk/34/07.md

3.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ በሕዝቅኤል በኩል ለእስራኤል መሪዎች መልዕክት መስጠቱን ቀጥሏል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ስለ እስራኤል ሰዎች እንደ በጎች መንጋ፣ የእስራኤል መሪዎችን ደግሞ ለመንጋው ግድ እንደማይላቸው እረኞች አድርጎ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የያህዌን ቃል ስሙ

ይህ ከያህዌ ልዩ መልዕክት ለማስተዋወቅ የዋለ ፈሊጥ ነው፡፡ "የያህዌን መልዕክት አድምጡ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በሕያውነቴ

"እኔ ሕያው እንደሆንኩ፡፡" ያህዌ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው ቀጥሎ የሚናገረው በእርግጥ እውነት መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ ይህ የከበረ ቃል መግቢያ መንገድ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "በክብሬ እምላለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ የጌታ የያህዌ ትዕዛዝ ነው

ያህዌ ራሱን በስሙ የሚገልጸው/የሚምለው፤ የተናገረው እርግጠኛ መሆኑን ለማሳወቅ ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 5፡11 ላይ እንዴት እንተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ጌታ ያህዌ የተናገረው ይህንን ነው" ወይም "እኔ ጌታ ያህዌ የተናገርኩት ይህ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

መንጋዬ ስለተዘረፈ እና በሜዳ ለሚገኝ አውሬ ምግብ ስለሆነ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በሜዳ ያሉ አውሬዎች ሁሉ መንባዬን ስለሰረቁ እና ስለበሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ዝርፊያ

የተሰረቁ ነገሮች

በሜዳ ያሉ አውሬዎች ሁሉ

እዚህ ስፍራ "ሁሉ" የሚለው በግ የሚበሉ የዱር እንስሳትን ሁሉ የሚያመለክት አጠቃላይ መገለጫ ነው፡፡ "በሜዳ የሚገኙ የዱር እንስሳት ሁሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

እረኛ ባለመኖሩ ምክንያት

"እረኛ ስለ ሌላቸው"

ከእረኞቼ አንዱም መንጋዬን አልተመለከተም

"ከእረኞቼ አንዱም መንጋዬን ለማግኘት አልሞከረም"

ራሳቸውን ጠበቁ

"ራሳቸው ተንከባከቡ" ወይም "ራሳቸውን መገቡ፣ ለራሳቸው እንክብካቤ አደረጉ"

የእኔን መንጋ አልጠበቁም

"የእኔን መንጋ አልመገቡም፣ መንጋዬን አልተንከባከቡም"