am_tn/ezk/34/01.md

4.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

በምዕራፍ 34፣ ያህዌ፣ የእስራኤል ህዝብ እንደ በግ መንጋ እንደሆኑ እና የእስራኤል መሪዎች ደግሞ መንጋውን እንደሚጠብቁ እረኞች ተደርገው ነገር ግን ድርሻቸውን ሳይወጡ እንደቀሩ ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የያህዌ ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢዩ ወይም ለህዝቡ የተናገረውን ነገር ለማስተዋወቅ የዋለ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ ይህንን መልዕክት ነናገረ" ወይም "ያህዌ እነዚህን ቃላት ተናገረ/ያህዌ እንዲህ አለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው ልጅ

"የሰብአዊ ፍጡር ልጅ" ወይም "የፍጥረታዊ ሰው ልጅ፡፡" እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ ብሎ የሚጠራው ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ እና ሀያል ነው፣ ሰዎች ግን እንዲህ አይደሉም፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ሟች የሆነ ሰው" ወይም "ሰብአዊ ፍጡር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

የእስራኤል ጠባቂ

የእስራኤል መሪዎች እረኞች እንደሆኑ ተደርጎ ተገልጸዋል፡፡ እረኛ መንጋውን እንደሚንከባከብ የህዝባቸው ጠባቂ እንዲሆኑ ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ "እንደ እረኞች የሆኑ የእስራኤል መሪዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እራሳቸውን ይንከባከቡ ነበር

መሪዎቹ ህዝቡን ከመጠበቅ ይልቅ የራሳቸውን ምቾት መጠበቃቸው የተገለጸው ራሳቸውን እንደሚጠብቁ ተደርጎ ነው፡፡ "ራሳቸውን ይመግባሉ፣ ራሳቸውንም ብቻ ይንከባከባሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እረኞች መንጋውን ሊጠብቁ አይገባምን?

ያህዌ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመበት መሪዎች ህዝቡን ባለመንከባከባቸው ሊገስጻቸው ነው፡፡ "እረኞች መንጋውን ሊመግቡ፣ ሊንከባከቡትም ይገባል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እናንተ ስቡን ተመገባችሁ… ሐር ለበሳችሁ

የእስራኤል መሪዎች እንደ መጠፎ እረኛ ከመንጋው ምርጡን እያረዱ የሚበሉና የበጉን ጸጉር እየለበሱ ለመንጋው ግን ገድ እንደማየላቸው ተደርጎ መገለጹ ቀጥሏል፡፡ "እናንተ ለመንጋው ግድ እንደሌለው የሰባውን እንደሚመገብ… ሱፉን እንደሚለብስ እረኛ ብቻ ናችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እናንተ ስቡን ተመገባችሁ

የሰባው ክፍል የሚገኘው ከበጎች እና ፍየሎች ነው፡፡ "የቡን እና ፍየሉን ስብ ክፍል ትመገባላችሁ" ወይም "እናንተ የበጎቹን እና ፍየሎቹን ምርጥ ክፍል ትመገባላችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሱፉን ትለብሳላችሁ

"ከበጎች የሚገኘውን ሱፍ ትለብሳላችሁ"

የሰባውን

"የሰባውን የበግ እና ፍየል ጠቦት"

ፈጽሞውኑ አትጠብቋቸውም

"መንጋውን አትመግቡም፣ እንክብካቤም አታደርጉለትም"