am_tn/ezk/33/32.md

2.2 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል ስለ እስራኤል ሰዎች መናገሩን ቀጥሏል፡፡

አንተ ለእነርሱ ደስ እንደሚየሰኝ መዝሙር ሆነህላቸዋል

እዚህ ስፍራ "አንተ" የሚለው የሚያመለክተው ሕዝቅኤልን ሲሆን፣ እርሱ ደግሞ የተናገረውን መልዕክት ይወክላል፡፡ ይህ የሕዝቅኤልን መልዕክት ደስ ከለሚያሰኝ ዝማሬ ጋር ያነጻጽራል፤ ይህም ማለት ሰዎች እርሱን መስማት ያስደስታቸዋል፣ ነገር ግን መልዕክቱን ለመታዘዝ ስፍራ አይሰጡም፡፡ "ቃሎችህ ደስ የሚያሰኝ ዝማሬ እንደሆነ አድርገው ያስባሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ደስ የሚያሰኝ ዝማሬ

ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "ውብ ዝማሬ" ወይም 2) "የፍቅር ዝማሬ" ወይም "ስለ ፍቅር የተዘመረ"

በክር የሙዚቃ ማሳሪያ በሚገባ የተጫወቱት

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አንድ ሰው በክር የሙዚቃ መሳሪያ በሚገባ የተጫወተው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የክር ሙዚቃ መሳሪያ

ሰዎች ሙዚቃ ለመጫወት የሚጠቀሙበት የክር ሙዚቃ መሳሪያ

ይህ ሁሉ በሚሆንበት ጊዜ

"ይህ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔር የተናገራቸው ነገሮች ሁሉ እንደሚፈጸሙ እና ሕዝቅኤል ስለ ነገሩ ለህዝቡ እንደተናገረ ነው፡፡

እነሆ!

እዚህ ስፍራ "እነሆ!" የሚለው ቃል ቀጥሎ ለሚሆነው ነገር ትኩረት ይሰጣል፡፡ "በእርግጥ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

በመሃላቸው ነቢይ እንዳለ

"እኔ አንተን ወደ እነርሱ በእርግጥ ነቢይ አድርጌ እንደ ላክሁህ"