am_tn/ezk/33/25.md

2.8 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ በእስራኤል ፍርስራሽ ላይ ስለሚኖሩ ሰዎች ለሕዝቅኤል መናገሩን ቀጥሏል፡፡

እናንተ ደም በላችሁ

በውስጡ ደም ያለበትን/ ደሙ ገና ከውስጡ ያልወጣን ስጋ መብላታቸው ተጠቅሷል፡፡ ያህዌ በስጋ ውስጥ ያለ ደም ተንጠፍጥፎ እንዲወጣ አዟቸው ነበር፡፡ "በውስጡ ደም ያለበትን ስጋ በላችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ዐይኖቻችሁን ወደ ጣኦቶቻችሁ አነሳችሁ

"ወደ ጣኦቶቻችሁ ተመለከታችሁ" ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "ጣኦቶቻችሁን አመለካችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሰዎችን ደም አፈሰሳችሁ

እዚህ ስፍራ "ደም" የሚወክለው የሰውን ህይወት ነው፡፡ ደም ማፍሰስ መግደል ለሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "ሰዎችን ገደላችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

በእርግጥ ምድሪቱን መውረስ ይገባችኋልን?

ያህዌ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመበት ህዝቡን ለመገሰጽ ነው፡፡ "ይህንን ምድር መውረስ አይገባችሁም!" ወይም "ይህ ምድር አይገባችሁም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በሰይፎቻችሁ ተማምናችኋል

እዚህ ስፍራ "ሰይፎች" የሚያመለክተው የጥቃት ተግባር መፈጸምን ነው፡፡ "የምትፈልጉትን ለማግኘት በሰይፎቻችሁ የጥቃት ተግባር ፈጽማችኋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

አስጸያፊ ተግባር ፈጽማችኋል

"እኔ በጣም የምጠላውን ተግባር አድርጋችኋል"

እያንዳንዱ ወንድ የጎረቢቱን ሚስት አርክሷል

የጎረቢቶቻቸውን ሚስቶች አብረው በመተኛት ማርከሳቸው ተጠቁሟል፡፡ "እያንዳንዱ ወንድ ከጎረቢቱ ሚስት ጋር ተኝቷል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)