am_tn/ezk/33/17.md

2.6 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለእስራኤላውያን በሕዝቅኤል በኩል መልዕክቱን መስጠቱን ቀጥሏል

የአንተ ህዝብ

እነዚህ የእስራኤል ሰዎች ናቸው፡፡ "የአንተ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሕዝቅኤልን ነው፡፡

የጌታ መንገድ… ተገቢ ያልሆኑ የእናንተ መንገዶች

ባህሪያት ወይም ድርጊቶች የተገለጹት አንድ ሰው የሚሄድበት መንገድ ወይም ጎዳና እንደሆኑ ተደርጎ ነው፡፡ "ይህ ጌታ ያደረገው… እናንተ ያደረጋችሁት ተገቢ ያልሆኑ ነገሮች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን እነዚህ የእናንተ መንገዶች ናቸው

"የእናንተ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእስራኤልን ሰዎች ነው፡፡ ይህ በሶስተኛ መደብ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ነገር ግን ይህ የእነርሱ መንገድ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)

ከጽድቁ ቢመለስ

ከዚያ በኋላ አንድ ነገር አለማድረግ የተገለጸው በአካል ከአንድ ነገር ዞሮ እንደ መመለስ ተደርጎ ነው፡፡ "ትክክለኛ የሆነውን ነገር ማድረግ ማቆም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በዚያው ውስጥ ሆኖ መሞት

"በኃጢአቱ ምክንያት መሞት"

ከክፉ ስራው ቢመለስ

ከዚያ በኋላ አንድ ነገር አለማድረግ የተገለጸው በአካል ከአንድ ነገር ዞሮ እንደ መመለስ ተደርጎ ነው፡፡ "ትክክለኛ የሆነውን ነገር ማድረግ ማቆም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእነዚያ ነገሮች ምክንያት

"ፍትሃዊ እና ትክክለኛ ነገር በማድረጉ ምክንያት"

የአንተ ህዝብ/ህዝብህ

እነዚህ የእስራኤል ሰዎች ናቸው

የእስራኤል ቤት

እዚህ ስፍራ "ቤት" የሚለው የሚወክለው ሰዎችን ነው፡፡ "የእሰስራኤል ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)