am_tn/ezk/33/12.md

2.1 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለእስራኤላውያን በሕዝቅኤል በኩል መልዕክቱን መስጠቱን ቀጥሏል

ጻድቁ ሰው ኃጢአት ቢሰራ የቀደመው ጽድቁ አያድነውም!

"ጽድቅ" የሚለው ረቂቅ ስም "ትክክለኛ" በሚለው ቅጽል ሊገለጽ ይችላል፡፡ ከእግዚአብሔር ቅጣት እንደማይተረፉ ተጠቁሟል፡፡ "ጻድቃን ሰዎች ኃጢአት ማድረግ ቢጀምሩ፣ አስቀድሞ የሰሩት ትክክለኛ ነገር እነርን ከመቅጣት አያቆመኝም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

የክፉ ሰው የቀደመ ክፋት እንዲጠፋ አያደርገውም

"ክፋት" የሚለው ረቂቅ ስም "ክፉ" በሚለው ቅጽል ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ክፉ ያሆነ ነገር ያደረገ ሰው በቀደመው ክፋቱ አይጠፋም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ጽድቁ ቢመለስ/ቢዞር

ሰውየው ያንን የሚያስበው አስቀድሞ ትክክለኛ ስለነበረ ነው፤ ቢበድል እንኳን ያህዌ እርሱን አያጠፋውም፡፡ "ጽድቅ" የሚለው ረቂቅ ስም "ትክክለኛ" በሚል ቅጽል ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አስቀድሞ በሰራቸው ትክክለኛ ነገሮች ላይ ቢጸና" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ኢፍትሃዊ ነገሮችን ቢያደርግ

"ክፉ የሆነውን ቢያደርግ" ወይም "ክፉ ነገሮችን ቢያደርግ"

እኔ አላስበውም

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "ስለዚያ ነገር አላስብም" ወይም "አላስታውስበትም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)