am_tn/ezk/33/07.md

2.7 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለሕዝቅኤል መናገሩን ቀጥሏል፡፡

የእስራኤል ቤት

እዚህ ስፍራ "ቤት" የሚለው የሚወክለው ሰዎችን ነው፡፡ "የእስራኤል ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ ከአፌ ቃሎቹን ትሰማለህ፣ ደግሞም በእኔ ምትክ ሆነህ ታስጠነቅቃቸዋለህ

እዚህ ስፍረ "አፍ" የሚለው የሚወክለው ያህዌ የተናገረውን ነገር ነው፡፡ "እኔ የምናገረውን መልዕክት አንተ ትሰማለህ፣ ከዚያም በእኔ ምትክ ሆነህ እነርን ታስጠነቅቃቸዋለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በእኔ ምትክ ሆነህ አስጠንቅቃቸው

"የእኔ ተወካይ ሆነህ አስጠንቅቃቸው" ወይም "የእኔን ማስጠንቀቂያ ስጣቸው"

ይህንን አታውጅ

"ይህንን አትናገር"

ስለ እርሱ መንገድ

"እርሱ የሚያደርግበት መንገድ" ወይም "እርሱ የሚያደርጋቸው ነገሮች" በሕዝቅኤል 7፡3 ላይ "የአንተ መንገዶች" የሚለው እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

ደሙን ከእጅህ እፈልጋለሁ

እዚህ ስፍራ "ደም" የሚወክለው የአንድን ሰው ሞት ነው፡፡ "ከእጅህ…እፈልጋለሁ" የሚለው ሀረግ አንድ ሰው ሀላፊነት አድርጎ መውሰድን/መጠየቅን የሚገልጽ ፈሊጥ ነው፡፡ "አንተን ለእርሱ ሞት ተጠያቂ አድርጌ እወስዳለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

እርሱ ምናልባት ከዚያ ይላል፣ ከመንገዱ ሳይመለስ ቢቀር

በተለመደ መንገድ ያደርገው የነበረውን ማድረግ ያቆመ አንድ ሰው የተገለጸው በአካል ዞሮ ወደ ኋላ መሄድ እንደጀመረ ተደርጎ ነው፡፡ "ክፉ ነገሮችን ማድረግን ሊያቆም ይችላል፣ እናም ክፉ ነገሮችን ማድረግ ባያቆም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የራስህን ህይወት ታድናለህ

"ራስህን በህይወት ትጠብቃለህ"