am_tn/ezk/33/05.md

2.3 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ለእስራኤላውያን በሕዝቅኤል በኩል መልዕክቱን መስጠቱን ቀጥሏል

ደሙ በእርሱ ላይ ነው

እዚህ ስፍራ "ደም" የአንድን ሰው ሞት ይወክላል፡፡ "በእርሱ ላይ" የሚለው ሀረግ ሰውየው ሃላፊነቱን ይወስዳል ለሚለው ፈሊጥ ነው፡፡ "ቢሞት የራሱ ጥፋት ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

የገዛ ህይወቱን ያተርፋል

"ራሱን ከሞት ይጠብቃል"

ሰይፍ በሚመጣበት ጊዜ

"ሰይፍ" የሚለው ቃል የጠላትን ሰራዊት ያመለክታል፡፡ "የጠላት ሰራዊት እየመጣ ሳለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ሰዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባለመደረጉ ምክንያት

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ደግሞም እርሱ ሰዎችን አላስጠነቀቀም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰይፍ መጣ ደግሞም ሳይመርጥ ህይወት ቀጠፈ

እዚህ ስፍራ "ሰይፍ" የጠላትን ሰራዊት ይወክላል፡፡ "የጠላት ሰራዊት መጥቶ ሁሉንም ገደለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ያ ሰው በራሱ ኃጢአት ይሞታል

"ያ ሰው በራሱ ኃጢአት ምክንያት ይሞታል"

የእርሱን ደም ከጠባቂው/ጉበኛው እፈልጋለሁ

እዚህ ስፍራ "ደም" የአንድን ሰው ሞት ይወክላል፡፡ "ደሙን ከእርሱ እፈልጋለሁ" የሚለው ሀረግ የአንድን ሰው ሀላፊነት የሚመለከት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "የዚያን ሰው ሞት የጉበኛው ጥፋት አድርጌ እውደዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)