am_tn/ezk/33/01.md

2.7 KiB

የያህዌ ቃል መጣ

ይህ እግዚአብሔር ለነቢዩ ወይም ለህዝቡ የተናገረውን ነገር ለማስተዋወቅ የዋለ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 3፡16 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ያህዌ ይህንን መልዕክት ነናገረ" ወይም "ያህዌ እነዚህን ቃላት ተናገረ/ያህዌ እንዲህ አለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው ልጅ

"የሰብአዊ ፍጡር ልጅ" ወይም "የፍጥረታዊ ሰው ልጅ፡፡" እግዚአብሔር ሕዝቅኤልን እንዲህ ብሎ የሚጠራው ሕዝቅኤል ሰው ብቻ መሆኑን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ እና ሀያል ነው፣ ሰዎች ግን እንዲህ አይደሉም፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 2፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ሟች የሆነ ሰው" ወይም "ሰብአዊ ፍጡር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

በማናቸውም ምድር ሰይፍ ይሆናል

"ሰይፍ" የሚለው ቃል ጥቃት የሚያደርስን የጠላት ሰራዊት ያመለክታል፡፡ እንደዚሁም ደግሞ "ምድር" በዚያ የሚኖሩ ሰዎችን ያመለክታል፡፡ "የማናቸውንም ምድር ሰዎች የሚያጠቃ ሰራዊት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱን ጠባቂ/ጉበኛ ማድረግ

"እርሱን እንደ ዘብ መሾም" ወይም "እርሱን ጠባቂ/ጉበኛ ማድረግ"

ሰይፍ ይመለከታል

እዚህ ስፍራ "ሰይፍ" የጠላትን ሰራዊት ይወክላል፡፡ "የጠላትን ሰራዊት ያያል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ትኩረት አትስጡ

"ማጠንቀቂያውን ቸል በሉ"

የእያንዳንዱ ደም በገዛ ራሱ ላይ ነው

እዚህ ስፍራ "ደም" ሞትን ይወክላል፡፡ "በገዛ ራሱ ላይ" የሚለው ሀረግ ያ ሰው ተጠያቂ ይሆናል ለሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "ቢሞቱ ተጠያቂነቱ የራሳቸው ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)