am_tn/ezk/32/31.md

1.6 KiB

ፈርኦን ይመለከታል/ያያል

ይህ ፈርኦንንነ ማንን እንደሚመለከት በመግለጽ ይበልጥ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡"ፈርኦን ከሌሎች አገራት የሆኑትን የሞቱ ሰዎች ሁሉ ይመለከታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ስለ አእላፋቶቹ ይጽናናል

ፈርኦን የሚጽናናው የሌሎች ታላላቅ ነገሥታት ሰራዊትም ጭምር በመገበላቸው መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ "መላው ሰራዊቱ የተገደለበት እርሱ ብቻ ባለመሆኑ ራሱን ያጽናናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በሰይፍ የተወጉ

በሕዝቅኤል 31፡17 ላይ "በሰይፍ የተገደሉ" የሚለው እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

በህያዋን ምድር ማሸበሪያ አደረግሁት

"ፈርኦን ገና በህይወት ሳለ፣ ሰዎችን መሸበሪያ አደረግሁት"

ባላተገረዙት መሃል ይጋደማል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሌሎች ባልተገረዙት መሃል ያጋድሙታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ ሚለውን ይመልከቱ)