am_tn/ezk/32/28.md

2.4 KiB

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

እናንተ… ትሰበራላችሁ

እዚህ ስፍራ "ትሰበራላችሁ" የሚለው የሚወክለው "መደምሰስን" ነው፡፡ ይህ በዐድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እኔ እደመስሳችኋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ እና ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

በ…መሃል

"በ…መካከል

ተወግተው የነበሩ

እዚህ ስፍራ "ተወግተው" የሚለው ቃል "ተገድለው" ለሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 32፡25 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ጠላቶቻቸው የገደሏቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በሰይፍ

ይህ የሚወክለው በጦርነት ውስጥ መሆንን ነው፡፡ "በጦር ሜዳ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ኤዶም ከነገሥታቷ እና መሪዎቿ ጋር በዚያ አለች

እዚህ ስፍራ "ኤዶም" የምትወክለው የኤዶምን ሰዎች ነው፡፡ "የኤዶም ሰዎች ከነገሥታቶቻቸው እና ከመሪዎቻቸው ጋር በሲኦል ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ጉድጓዱ

"ጉድጓዱ" የሚለው የሚያመለክተው መቃብርን ነው፣ ምክንያቱም መቃብር ወደ ሞት ዓለም መግቢያ ተደርጎ ይታሰብ ነበር፣ እንደዚሁም ደግሞ ጉድጓድ ያንን ዓለም ይወክላል፡፡ ይህ በሕዝቅኤል 32፡25 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)